Skip to main content

Amharic

የሴቶች እና ወላጅ ሰዎች መረጃ በራሪ ወረቀት፡

“ማተርኒቲ ኢን ከለር” ፕሮጀክት

ፕሮጀክቱ ምንን የሚመለከት ነው?

ይህ የሳልፎርድ ዩኒቨርሲቲ እና የማንችስተር ዩኒቨርሲቲ ኤን ኤች ኤስ ፋውንደሽን በጋራ የሚያካሂዱት ፕሮጀክት ነው። ጥቁር፣ ቡናማ እና የተለያየ የዘር የቈዳ ቀለም ባላቸው ሴቶች እና ወላጅ ሰዎች (እና/ወይም ልጆቻቸው) የተለመዱ የወሊድ እና ድሕረ ወሊድ ሁኔታዎችን የህክምና ፎቶግራፎችን በማሰባሰብ ላይ እንገናኛለን። እነዚህ ምስሎች በዲጂታላዊ መጽሓፍት ውስጥ የሚካተቱ ሲሆን በዩኒቨሪሲቲዎች፣ አዋላጆች፣ የአዋላጅነት ተማሪዎች እና ሌሎች የጤና እንክብካቤ ባለሙያዎች የነጻ ዲጂታላዊ የመማሪያ ማጣቀሻ ሆነው እንዲያገለግሉ የሚቀርቡ ናቸው።

ይህ ፕሮጀክት ለምን ይከናወናል?

ከተለያዩ ዘሮች የመጡ ሴቶች፣ ወላጅ ሰዎች እና ልጆቻቸው ከነጮች ጋር ሲወዳደሩ፡ በወሊድ እንክብካቤ ረገድ ያነሱ ውጤቶች እና ልምዶች ይኖሯቸዋል።

አንደኛው ምክንያት የወሊድ ሰራተኛ አባላት ጠቆር ያለ የቄዳ ቀለም ባላቸው ላይ የሚገኙ አንዳንድ የጤና ሁኔታዎችን መለየት ስለሚያስቸግራቸው ነው ምክንያቱም የህክምና መጽሃፍት እና የስልጠና መገልገያዎች ነጣ ያለ ቈዳ ብቻ ስለሚጠቀሙ ነው።

ይህ ፕሮጀክት፡ጥቁር፣ ቡናማ እና የተለያየ የዘር የቈዳ ቀለም ባላቸው ላይ የሚታዩ የለመዱ የእርግዝና፣ ወሊድ እና ድሕረ ወሊድ ሁኔታዊች ላይ ለወሊድ አባላት የሚሰጠው ስልጠና እንዲሻሻል ትኩረት ያደርጋል። እነዚህ ስእሎች አዋላጆች፣ ነርሶች፣ ዶክተሮች እና ቤተሰቦችን ማስተማር እና ማሰልጠን ላይ ጥቅም ይውላሉ በዚህም አባላት ሁኔታዎችን እንዲለዩ እና የበለጠ ደህንነት ያለው እና የበለጠ ውጤታማ እንክብካቤ እንዲያቀርቡ ያስችላቸዋል። ማጣቀሻዎቹ በተጨማሪ ሴቶች እና ወላጅ ሰዎችን እኛ ቤተሰቦቻቸው፡ አስፈላጊ ሁኔታዎችን እንዲለዩ ያስችላል በዚህም የቅድሚያ ግንዛቤ፣ ማረጋገጫ እና ግዜውን የጠበቀ እንክብካቤ ማግኘት ላይ ያግዛቸዋል።

ብሳተፍ ምንድነው የሚሆነው?

  • እናንተ ወይም ልጃችሁ ሁኔታዎች ካሉባችሁ እና ይህም በፎቶ እንዲነሳ ከፈለጋችሁ የወሊድ ህክምና ቡድን አባል ስለ አሳያችሁት ፍላጎት ምስጋናቸውን ይገልጹላችኋል እንዲሁም ስለ ፕሮጀክቱ ይገልጹላችኋል ማንኛውም ጥያቄ ካላችሁም ይመልሱላችኋል።
  • የእናንተ (ወይም የልጃችሁን )ስእል እንዲወሰድ እና በጥብቅ እንዲቀምጥ  መረጃ ላይ የተመረኰሰ ፈቃድ  እንድትሰጡ ትጠየቃላችሁ።
  • ለመሳተፍ ፈቃደኛ ከሆናችሁ፡  የህክምና ፎቶግራፍ እና የህክምና ምስል ቅንብር አገልግሎት አባል  ከማንችስተር ዩኒቨርሲቲ ኤን ኤች ኤስ ትረስት ፈንድ ይመጣ እና ፎቶዎቹን ያነሳል።
  • በተጨማሪም የምትሰጡት ፈቃድ፡ ስእሎቹን  ለህትመት መጠቀምን ያጠቃልላሉ (ለምሳሌ በመማሪያ መጽሓፍት፣ የትምህርት ማጣቀሻዎች ወይም የወደፊት ምሁራዊ ጽሑፎች)።

ሁሉም ስእሎች የህክምና መዝገባችሁ አካል ይሆናሉ ግን ፈቃዳችሁን አንዴ እንደሰጣችሁ ለትምህርታዊ ህትመት ወደ ሳልፎርድ ዩኒቨርሲቲ እንልካቸዋለን። እናንተን ሊያሳውቁ የሚችሉ መረጃዎች አይጋሩም ወይም አይታተሙም።

ምን ዓይነት ስእሎች ናቸው የሚነሱት?

ፎቶግራፎች የሚከተሉትን የተለመዱ ሁኔታዎች ሊያጠቃልሉ ይችላሉ ግን እነዚህ ብቻ ላይሆኑ ይችላሉ፡

  • የእርግዝና ለውጦች (ለምሳሌ የሆድ ላይ ምልክቶች፣ ቫሪኰስ ቬይን (የእግር ላይ ደምስሮች)፣ እብጠት)
  • ጡት ማጥባት (ለምሳሌ፡ አቀማመጥ፣ ቅርበት፣ የጡት ላይ ቁስሎች፣ የጡት ጫፍ ቁስሎች፣ የተደፈኑ መተላለፍያዎች)
  • ሆስፒታል ውስጥ ህክምና ወይ ድጋፎች እየተደረገ ባለበት ቈዳ ላይ የሚፈጠሩ ለውጦች  (ለምሳሌ ከሚተከሉ ቱቦዎች ጋር የተያያዙ ለውጦች፣ በግፊት የሚፈጠሩ ቁስሎች እና አልሰሮች፣ ሰንበር ወይም ደም በቈዳ ስር መፍሰስ)
  • የድሕረ ወሊድ ለውጦች (የቀዶ ጥገና ቁስል ጠባሳ ወይ ስፌቶች መዳን፣ ኢንፌክሽኖች፣ የሆድ ላይ ጡንቻዎች መለያየት)
  • የድሕረ ወሊድ ሁኔታዎች (ጃውንዲስ፣ ሰማያዊ ነጠብጣቦች፣ ሽፍታዎች፣ የወሊድ ምልክቶች እና ጠባሳዎች)
  • የቅድመ ወሊድ፣ የድሕረ ወሊድ ወዲያውኑ እና የድሕረ ወሊድ የዘወትር እንክብካቤዎች ስእሎች።

ሁሉም ስእሎች፡ የኤን ኤች ኤስ ግል ክብር፣ የግል መብት ፈቃድ እና ሚስጥራዊነት ፖሊሲዎችን በመከተል፡ በሙያዊ መንገድ እና በጥንቃቄ ይነሳሉ።

መረጃዎቼ እና ስእሎቹ እንዴት ይያዛሉ?

  • ስእሎቹ በማንቸስተር ዩኒቨርሲቲ ኤን ኤች ኤስ ፋውንደሽን ትረስት የሚያዘው ጥብቅ  ህክምናዊ ማህደር  አካል ይሆናሉ።
  • በተጨማሪም (ማንነት ሳይገለጥባቸው) “ማተርኒቲ ኢን ከለር” ፕሮጀክት ውስጥ እንዲካተቱ ለሳልፎርድ ዩኒቨርሲቲ ይጋራሉ።
  • ሁሉም መረጃዎች በኤን ኤች ኤስ  የመረጃ ጥበቃ ሕግ 2018  እና  የዩኬ አጠቃላይ መረጃ ጥበቃ መመሪያ (ጂዲፒአር) ፖሊሲዎች ጥበቃ ይደረግለታል
  • የግል መረጃችሁ (ስም፣ አድራሻ፣ የትውልድ ቀን ወዘተ) ለዚህ ፕሮጀክት አይተላለፉም።

ፎቶዎቹ እንዴት ነው የሚነሱት?


የህክምና ፎቶግራፍ ቡድን የህክምና ስእሎችን የማንሳት ልዩ ሞያ ያላቸው ናቸው። ሁሉም ጥረት መነሳት በሚገባው ሁኔታ ላይ እንዲያተኩር ማድረግ ነው ስለዚ መለያ የሚሆኑ መልኮች (ለምሳሌ ፊታችሁ) አይካተቱም። ይሁን እንጂ፡ አንዳንድ ገጽታዎች ለምሳሌ የወሊድ ምልክቶች፣ ትርፍ ስጋዎች ወይ ንቅሳቶች ስእሉ ላይ ሊታዩ ይችላሉ ይህ ማለት ማንነት ሊታወቅባቸው የሚችሉ ምልክቶችን ሙሉ በሙሉ እንደምናስወግድ መተማመኛ ማቅረብ አንችልም።

ፈቃዴን ከቀየርኩስ?

ፎቶግራፎቹ ከተነሱ በኋላ እስከ 56 ቀናት  ባሉት ግዜዎች ውስጥ ፈቃዳችሁን ማስወጣት ትችላላችሁ። ከዚህ ግዜ በኋላ ስእሎቹ ማንነት የማይገለጽባቸው ሆነው ይዘጋጃሉ እንዲሁም ለህትመት ይላካሉ ስለዚህ እንዲወጡ ማድረግ አይቻልም።

መሳተፌ እንክብካቤዬ ላይ ተጽእኞ ይፈጥራል?

አይ። በፈቃደኝነት ነው በፕሮጀክቱ ላይ የሚሳተፉት። ላለመሳተፍ መወሰን እንክብካቤያችሁ ላይ በምንም መንገድ ተጽእኖ አይፈጥርበትም።

ይህን ፕርጀክት በተመለከተ ማንኛውም ጥያቄ ካለኝ ማንን ላገኝ ይገባል?

ፕሮጀክቱን በተመለከተ ማንኛውም ጥያቄዎች ወይ ስጋቶች ካሏችሁ መጀመሪያ ላይ ደሪን ወብ ን/ወይ ካይሊ ዋትሰንን ጠይቁ እና ጥያቄዎቻችሁን ለመመለስ የተቻላቸውን ያደርጋሉ።

ግዜ ወስዳችሁ ይህን በራሪ ወረቀት በማንበባችሁ እና በ”ማተርኒቲ ኢን ከለር” ፕሮጀክት ላይ ለመሳተፍ በማሰባችሁ እናመሰግናለን። ተሳትፏችሁ፡ የተለያየ ዘር ባላቸው ቤተሰቦች የወሊድ እንክብካቤ እና ውጤቶች ላይ መሻሻል እንዲመጣ ያግዛል።

University of Salford
Manchester University NHS Foundation Trust